Welcome to Nifas Silk Lafto Subcity Peace and Security Office!       እንኳን ወደ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ ክ/ከተማችን በህዝብ ተሳትፎና ባለቤትነት ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባት፤ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ለኑሮ፣ ለስራ እና ለመዝናኛ ተመራጭ እንድትሆን ይተጋል!
image
image
image
image
image

የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አካሄደ

ሀምሌ 6, 2018
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አካሄደ። የችግኝ ተከላ መርሀ ግበሩ በክፍለ ከተማው ወረዳ 8 ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ዘላቂ ማረፊያ ቅጥር ጊቢ ውስጥ የተካሄደ ሲሆን የ2017 የአረንጓዴ አሻራ እቅድን ስኬታማ እንዲሆን ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል። መርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት መልዕክት የስተላለፉት የብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቱ ደሴ ፥ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ባለፉት ሰባት ዓመታት የኢትዮጵያን የደን ሽፋን በማሳደግ ለአረንጓዴ ኢትዮጵያ ዕውን መሆን ከፍተኛ ድርሻ ማበርከቱን አውስተዋል፡፡ አክለውም የአረንጓዴ አሻራ ሀገራዊ የልማት ጥሪ በመሆኑ በችግኝ ተከላው የተሳተፉ አካላት በአንድነትና በጋራ ለሀገር ልማት መሰለፋቸው የሚያስመሰግን መሆኑን ያመለከቱት ኃላፊው፣ በቀጣይም ከችግኝ መትከል ባሻገር የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ የጋራ ኃላፊታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የክፍለ ከተማው ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረጄ ድሪብሳ በበኩላቸው በችግኝ ተከላው ለተሳተፉ አካላት ምስጋና በማቅረብ ሰላምና ጸጥታ ከማስከበር ጎን ለጎን ማህበራዊ ሀላፊነት መወጣት እንደሚገባ ገልጸዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቱ ደሴ ፣ የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ድላየሁ ታምሬን ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮችን ጨምሮ የፀጥታ አካላትና ሰላም ሰራዊት አባላትም በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ተሳትፈዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ