Welcome to Nifas Silk Lafto Subcity Peace and Security Office!       እንኳን ወደ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ ክ/ከተማችን በህዝብ ተሳትፎና ባለቤትነት ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባት፤ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ለኑሮ፣ ለስራ እና ለመዝናኛ ተመራጭ እንድትሆን ይተጋል!
ዜና | Oduu | News
በክፍለ ከተማው "የሥነ- ምግባርና የሞራል ዕድገት ለሀገር ህልውና" በሚል መሪ ሃሳብ ከወጣቶች ጋር ውይይት መድረክ ተካሄደ።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ "የሥነ- ምግባርና የሞራል ዕድገት ለሀገር ህልውና" በሚል መሪ ሃሳብ ከወጣቶች ጋር ውይይት መድረክ ተካሂዷል። የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ከወጣቶች ክንፍ፣ ከወጣቶች ማህበር እና ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ጋር በጋራ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ከሁሉም ወረዳዎች ለተውጣጡ ወጣቶች በሰላም እሴት ግንባታ ዙሪያ መነሻ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቱ ደሴ ውይይቱ ወጣቶችን የሰላም ግንባታ ዋነኛ አካል አድርጎ በማሳተፍ ረገድ ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቁመው በወጣትነት ዕድሜ ክልል ያሉ ዜጎች ጊዜያቸውን በአግባቡ በመጠቀም ለሃገር ልማት ጠንክረው ማስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል። አቶ መብራቱ አክለውም ወጣቶች ስራ ሳያማርጡ በተገኘው የስራ ፀጋ ላይ ተሰማርተው ከራሳቸውም አልፈው ለሌላው ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረጀ ድሪብሳ ሀገርን ለማስቀጠል ተተኪ ወጣት ትልቁ ሚና እንዳለው ጠቁመው ወጣቱ ሙያዊ ስልጠናዎችን ወስዶ በአገር ግንባታ ላይ ንቁ ተሳታፊ በመሆን ሃገራዊ ኃላፊነቱን መወጣት እንደ አለበት ተናግረዋል። የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙባረክ ደሊል፣ ወጣቶች በሰላም እሴት ግንባታ መጎልበት ዙሪያ ያላቸው ሚና የጎላ መሆኑን ገልፀው የሰላም ግንባታ ጥረቶችን በማጠናከር ረገድ ሃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዋዩ አስተዳደር የአንድ ማዕከል የሰላም ሰራዊት ስምሪት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በአንድ ማዕከል ስምሪቱም ላይ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቱ ደሴ ፣የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሸዋንግዛው ሽመልስን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችና የፀጥታ አካላት በተገኙበት ስምሪት ተሰጥቷል ። በስፍራውም ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቱ ደሴ የሰላም ሰራዊቱ በየብሎኩ ለሰላም ዘብ እንዲቆም መልዕክታቸውን በማስተላለፍ የሰላም ሰራዊት አባላትን አበረታተዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ የግል ጥበቃ ኤጀንሲ አባላት እና ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ጥበቃዎች ስልጠና ተሰጠ

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ ለግል ጥበቃ ኤጀንሲ አባላት እና ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ጥበቃዎች ስልጠና ሰጥቷል። ስልጠናው የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጋር በትብብር የተዘጋጀ ነው። የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ አቶ ጌታሁን አበራ የከተማውን ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ ለማድረግና ሰላምና ፀጥታ ለማስፈን ማህበረሰቡን የሰላም ባለቤት ማድረግ ይገባል ብለዋል። ህብረተሰቡና ባለድርሻ አካላት ከመደበኛ የፀጥታ አካሉ ጋር ተቀናጅተው ከመስራት ባሻገር ዘመናዊ ቴክኖሎጂ (ሲሲቲቪ ካሜራ) በመጠቀም የወንጀል ምጣኔን መቀነስ እንደሚገባ ተናግረዋል። የሰላምና የፀጥታ ጉዳይ ለመንግስት ብቻ የሚተው አይደለም ያሉት አቶ ጌታሁን የግል የጥበቃ ኤጀንሲዎችም የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ አካባቢያቸውን በንቃት መጠበቅ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረጄ ድሪብሳ አንዳንድ የጥበቃ ኤጀንሲዎች የተቋቋሙበትን ዓላማ ወደ ጎን በመተው ከቀጠሯቸው የጥበቃ አባላት መካከል በሌላ እኩይ ተግባር ላይ እየተሰማሩና ወንጀሎች እየተፈፀሙ በመሆኑ ኤጀንሲዎች የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው ገልፀዋል። ያለ በቂ ዋስትና ቅጥር መፈፀም እንዲሁም የአንድ አከባቢ ሰዎችን በጥበቃ ስራ ላይ ማሰማራት ለወንጀሉ መባባስ ዋነኛ ምክንያት መሆኑንም አንስተዋል። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል ኃላፊ ኮማንደር ጌታቸው አለነ ወንጀሎችን አስቀድሞ መለየትና መከላከል በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ በተለይም በመኖሪያና በስራ አካባቢዎች የሚደረጉ ጥበቃዎችን ይበልጥ እያጠናከሩ መሄድ እንደሚገባ ተናግረዋል። የጥበቃ ኤጀንሲዎች ከሰራዊቱ በጡረታና በክብር የተቀነሱና በፀጥታ ስራ ላይ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው መሆኑን ጠቅሰው ይህን ልምድ ተጠቅሞ በተቋማት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን መቀነስ ይገባል ብለዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
ለ6ኛ ኮርስ ለአዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላት የንድፈ ሀሳብ ስልጠና ተሰጠ።

ላፍቶ፣ ታህሳስ፣ 21/2018:- በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ለ6ኛ ኮርስ ለአዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላት የንድፈ ሃሳብ ስልጠና ሰጥቷል። በእለቱም የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ ጨምሮ ሌሎች አመራሮችና የፀጥታ አካላት እንዲሁም አዲስ ምልምል ሰላም ሰራዊት አባላት ተገኝተዋል። የንድ ሃሳብ ስልጠናው የሰላም ምንነትና ሃገር ወዳድነት የሰላም ሰራዊት አደረጃጀት ደንብና መመሪያ እንዲሁም ወንጀል መከላከል በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው። መርሃ-ግብሩን ያስጀመሩት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ ባለፉት ዓመታት የሰላም ሰራዊት አባላት በክፍለ ከተማው የሚከናወኑ የተለያዩ የልማትና የመልካም አስተዳደር እንዲሁም የበጎ ፍቃድ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ እያደረጉ ያለው ተሳትፎ የጎላ መሆኑን አንስተዋል። ከዚሁ ተግባር ጎንለጎን የሰላም ሰራዊት አባላት ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የአካባቢውንና የህብረተሰቡን ሰላም በማስጠበቅ ረገድ በርካታ ስራዎች መስራታቸውን ገልፀዋል። የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረጄ ድሪብሳ የአዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላት በንድፈ- ሃሳብና በመስክ የሚሰጠውን ስልጠና ስነ-ምግባር በተሞላበት ሁኔታ በመከታተልና አቅማቸውን ማጎልበት እንዳለባቸው ተናግረዋል። ስልጠናው ለ10 ቀናት የንድፈ ሃሳብና የመስክ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑን ገልፀው የተሰጣቸውን ሰላም የማስጠበቅ ተልዕኮ በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው አፅንኦት ሰጥተዋል። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ኃላፊ ኮማንደር ኪዳኔ አያና አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት ለፀጥታ አካላት አጋዥ ሃይል በመሆን የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ ሃገራዊ ሃላፊነቱን መወጣት አለበት ሲሉ ተናግረዋል። የ6ኛ ኮርስ አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላት በበኩላቸው የንድፈ ሃሳብና የተግባር ስልጠናውን በአግባቡ ተከታትለው ለፀጥታ ስራው ተደማሪ አቅም እንደሚሆኑ ተናግረዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አካሄደ

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አካሄደ። የችግኝ ተከላ መርሀ ግበሩ በክፍለ ከተማው ወረዳ 8 ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ዘላቂ ማረፊያ ቅጥር ጊቢ ውስጥ የተካሄደ ሲሆን የ2017 የአረንጓዴ አሻራ እቅድን ስኬታማ እንዲሆን ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል። መርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት መልዕክት የስተላለፉት የብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቱ ደሴ ፥ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ባለፉት ሰባት ዓመታት የኢትዮጵያን የደን ሽፋን በማሳደግ ለአረንጓዴ ኢትዮጵያ ዕውን መሆን ከፍተኛ ድርሻ ማበርከቱን አውስተዋል፡፡ አክለውም የአረንጓዴ አሻራ ሀገራዊ የልማት ጥሪ በመሆኑ በችግኝ ተከላው የተሳተፉ አካላት በአንድነትና በጋራ ለሀገር ልማት መሰለፋቸው የሚያስመሰግን መሆኑን ያመለከቱት ኃላፊው፣ በቀጣይም ከችግኝ መትከል ባሻገር የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ የጋራ ኃላፊታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የክፍለ ከተማው ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረጄ ድሪብሳ በበኩላቸው በችግኝ ተከላው ለተሳተፉ አካላት ምስጋና በማቅረብ ሰላምና ጸጥታ ከማስከበር ጎን ለጎን ማህበራዊ ሀላፊነት መወጣት እንደሚገባ ገልጸዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቱ ደሴ ፣ የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ድላየሁ ታምሬን ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮችን ጨምሮ የፀጥታ አካላትና ሰላም ሰራዊት አባላትም በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ተሳትፈዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት በደንብ ቁጥር 156/2016 ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

ላፍቶ፣ ነሃሴ 2/2017:- የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት በደንብ ቁጥር 156/2016 ዙሪያ ለዘርፉ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራርና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል። የግንዛቤ መድረኩ ዋና ዓላማ ተቋሙ ቀጣይ ለሚያከናውነው የሰራተኛ ሪፎርም ሰራተኛው በቂ እውቀት እንዲኖረው የሚያስችል ነው ተብሏል። በዕለቱ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረጄ ዲሪብሳ ሪፎርሙ በዋናነት ክፍት የሆኑ የስራ መደቦች በሰው ኃይል እንዲሟሉና ባለሙያውሞ በባህሪና በክህሎት ብቃቱ ተመዝኖ ተቋማዊ ውጤታማነት እንዲረጋገጥ የሚያስችል ነው ብለዋል። በተጨማሪም ለስራ እንቅፋት የሆኑ ደንቦችና መመሪያዎችን በማስተካከል ተቋሙ በቴክኖሎጂ በመዘመን የተገልጋዮችን የአገልግሎት እርካታን ለመጨመር ፋይዳው የጎላ መሆኑን አንስተው ሰራተኛው በደንብና በመመሪያዎቹ ዙሪያ ተገቢውን ግንዛቤ በመያዝ በአፈፃፀም ሂደት ከሚኖሩ ብዥታዎች ነፃ ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል። በማጠቃልያውም ስለ ሰራተኞች ድልድል መመሪያ ለተነሱ ጥያቄዎችና ሀሳቦች ግልፀኝነት መፍጠር ተችሏል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
"Biyya Abbootiin keenya aarsaan nuuf tursiisan cichoominaan dhalootaaf nidabarsina" hirmaattota marii paanaalii

Biyya Abbootiin keenya aarsaa baay'een nuuf tursiisan Cichoominaan dhalootaaf nidabarsina jechuun hirmaattotni marii paanaalii Kutaa Magaalaa Nifaas Silki Laaftoo himan. Kutaa Magaalaa Nifaas Silki Lasftootti Qaammee1 guyyaa cichoominaa" bu'uura cimaa biyya jabduuf" dhaadannoo jedhuun mariin paanaalii geggeeffame. Guyyaa kanas miseensotni qaamoleen nageenyaa garaagaraa,abbootiin amantaa,Jaarsoliin biyyaa akkasumas kutaaleen hawaasaa garaa garaa argamaniiru. Marii paanaalii geggeeffameenis sanada dhiyaate ka'umsa godhachuun waliigaltee biyyaalessaa uumuu Marii paanaalii kana irratti sanada dhiyaate bu’uura godhachuun hirmaattonni kun dhimmoota waliigaltee biyyaalessaa yeroo waliin deemu uumuu fi biyya abbootiin keenya aarsaan asiin gahan cichoominaan dhaloota dhufuuf darbuu akkaataa itti dandeessisu irratti hirmaattonni xiyyeeffataniiru. Ityoophiyaan dhiigaa fi lafee abbootii ishee irratti ijaaramte sadarkaa ol’aanaa irratti ijaaramtee tokkummaa fi hamilee ijaarsa Hidha Haaromsaa keessatti mul’ate daran cimuu akka qabdu ibsameera. Waltajjicharratti ergaa kan dabarsan Itti Gaafatamaan Waajjira Nageenyaa fi Tasgabbii BKutaa Magaalichaa Obbo Darajjee Dirribsaa, Bu’uura cimaa yoo qabaanne, biyya cimtuu ni qabaanna akkasumas biyya walirkaa fudhinsa dhalootaan asgeesse itti fufsiisuu qabna jedhaniiru. Obbo Darajjeen itti dabaluudhaan biyyi keenya aarsaa guddaa dhiigaan bahe ta'uu ibsanii, bu'uura jabaa irratti ijaaruuf cichuu qabna jedhan. Kutaa Magaalichaatti Itti Aanaan Komishinaraa Komishinar Shimellis Shiferaaw toophiyaan biyya waggootan darban bu’aa ba’ii hedduu keessa darbitee cimtee turte ta'uu ibsanii, dhaloonni kun seenaa kana itti fufuu qaba” jedhan. Gootummaan karaa ammayyaa ta'een of guddisuu fi ergama nuuf kenname keessatti bu'aa galmaan gahuu akka ta'e eeranii, Hojiiwwan gama hundaan hojjetaman hunda gahumsaan raawwachuu qabna jedhaniiru.

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
ከበዓላት ጋር በተያያዘ ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሬ እንዳይከሰት በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከመጪው አዲስ ዓመት በዓል ጋር በተያያዘ ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሬ እንዳይከሰት በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል። የኑሮ ውድነትና ገበያ ማረጋጋት ግብረ ሃይል በዛሬው ዕለት በበዓላት ወቅት ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሬን መከላከል የሚያስችል ውይይት አካሂዷል። በዚህም በዓላቶች ላይ ሊፈጠሩ ይችላሉ ተብለው የሚገመቱ የዋጋ ጭማሪ፣ የገበያ አለመረጋጋት፣ መሰረታዊ ፍጆታዎችን በሚደብቁ ነጋዴዎች፣ የእሁድ ገበያና ሸማች ማህበራት ላይ በስፋት ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባ የሚያሳዩ ነጥቦች ተነስተዋል። የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረጄ ዲሪብሳ የገበያ ማረጋጋትና የኑሮ ውድነት የሚቀንሱ ስራዎችን ስንሰራ ለበዓላትና ለአንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ቀጣይነት ያለው ስራ መስራት ይገባል ብለዋል። አቶ ደረጄ አክለውም በዓላቱን ምክንያት በማድረግ ሊከሰት የሚችል የዋጋ ጭማሬን ከመከላከል ባሻጋር ለፀጥታ ስጋት የሆኑ ችግሮችን በተገቢው ለይቶ በቅንጅትና በትብብር መስራት ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። የክፍለ ከተማው ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መኮንን ዘነበ በመጪው መስከረም ወር ተከታታይ በዓላት በመኖራቸው ይህን ተከትሎ የፍጆታ ሸቀጦች ላይ የአቅርቦት ችግርና የዋጋ ጭማሬ እንዳይከሰት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። ከዚህ አንፃር ከሸማች ማህበራት፣ ከአርሶ አደሮች፣ ከጥቃቅን አንቀሳቃሾች፣ ከአቅራቢዎችና ከአምራቾች ጋር በቅርበት በመስራት በእሁድ ገበያ መዳረሻ ስፍራዎችና በባዛሮች ላይ ምርቶች በስፋትና በጥራት ቀርበው ገበያውን እንዲያረጋጉ እየተደረገ ነው ብለዋል። በመጨረሻም ቀጣይ የሚከበሩ በዓላት ጋር ተያይዞ ስለሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ የስራ አቅጣጫ ተቀምጧል።

image
image
image
image